BBC News, አማርኛ - ዜና
BBC News Amharic Top Stories
በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በደረሰ የጀልባ አደጋ 16 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ሞቱ
በሁለት ሳምንት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. ሰባ ሰባት ኢትዮጵያውያንን ይዛ ከየመን ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰምጣ ሴቶች እና ሕጻናትን ጨምሮ 16 ሰዎች መሞታቸውን በጂቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የመንግሥታቱ ድርጅት የፍልሰተኞች ተቋም አስታወቁ።
ከአላማጣ እና የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን ተመድ አስታወቀ
ግጭት በተነሳባቸው የአላማጣ ከተማ፣ ዛታ እና ኦፍላ የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ተፈናቃዮቹ የተጠለሉባቸውን የዞን ባለስልጣናት ዋቢ አድርጎ ጽህፈት ቤቱ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት 42 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ እንዲሁም 8300 የሚሆኑት ደግሞ በሰቆጣ እና ዋግ ኽምራ ዞኖች ተጠልለዋል ብሏል።
በደቡብ ጎንደር አምስት ሰዎች ሲገደሉ 18 ቤቶች መቃጠላቸውን ተጎጂዎች እና የዐይን እማኞች ተናገሩ
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና በተባለ ‘የቀበሌ ከተማ’ ባለፈው ሰኞ ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም. በፋኖ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተካሄደ ግጭትን ተከትሎ ነዋሪዎች መገደላቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።
አርሰናል ከቼልሲ ማን ያሸንፋል? የሊጉ ጨዋታዎች ግምት
አርሰናል በሜዳው ቼልሲን የሚያስተናግድበት የሳምንቱ አጋማሽ ጨዋታ በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ላይ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል? ጉዲሰን ፓርክ ላይ በተካሄዱት ያለፉት 11 ጨዋታዎች ሊቨርፑል ማሸነፍ የቻለው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። በዚህ ሳምንትስ? የሊጉ የሳምንቱ አጋማሽ ከዛሬ ጀምሮ የሚከናወኑ ሲሆን፣ የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የእነዚህን ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል?
በማሌዥያ ሁለት ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች በልምምድ እያሉ ተጋጭተው አስር ሰዎች ሞቱ
ሁለት የማሌዥያ አየር ኃይል ሄሊኮፕተሮች ለወታደራዊ ትዕይንት በልምምድ ላይ እያሉ መጋጨታቸውን ተከትሎ አስር ሰዎች ሞቱ።
ዩናይትድ ኪንግደም ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅዷ ሕግ ሆኖ ወጣ
በዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ላለፉት ወራት እጅግ ሲያወዛግብ የነበረው ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ ህግ ሆኖ ሊወጣ ነው።
በእስራኤል ጥቃት ከተገደለች ፍልስጤማዊት እናት ማህጸን ልጇን ማትረፍ ተቻለ
ፍልስጤማዊቷ ሳብሪን ለወራት ያህል የተሸከመቻትን ህጻን አይኗን ሳታይ እና ሳታቅፍ ተገደለች። የሰባት ወር ተኩል ነፍሰ ጡር ነበረች።
ወሲባዊ ይዘት ላላቸው ፎቶዎች ከፍሏል የተባለው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ከሥራ ለቀቀ
ከአንድ ታዳጊ ወሲባዊ ይዘት ያለው ፎቶግራፍ እንዲካክለት ገንዘብ ከፍሏል በሚል መወዛገቢያ ሆኖ የነበረው ታዋቂው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሂው ኤድዋርድስ ከሥራ ለቀቀ።
የ3 ዓመት ሕፃናት በኢንተርኔት ለወሲባዊ ብዝበዛዎች እየተጋለጡ መሆኑን አንድ ድርጅት አስጠነቀቀ
ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን የተሰኘው ተቋም በአውሮፓውያኑ 2023 ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ሕፃናት በኢንተርኔት አማካይነት ወሲባዊ ብዝበዛ ደርሶባቸዋል ብሏል።
ቪዲዮ, ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ቡና ለጤና እና ለዓለም ሥልጣኔ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በጥቂቱርዝመት, 6,19
በዓለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በየዕለቱ ቡና ይጠጣሉ። ቡና ቢያንስ ላለፉት 1500 ዓመታት እንደተጠጣ ይነገራል። ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ይህ ፍሬ ዛሬ ዓለም ላለችበት ዕድገትም የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት ምሁራን ይጠቅሱታል። በሌላ በኩል በሰውነታችን ውስጥ የተለያዩ በሽታዎችን በመከላከልና አዕምሮን በማንቃት አስተዋጽኦ እንዳለው የጤና ሙያተኞች ይመሰክራሉ። ቢቢሲ በዚህ ቪዲዮ ስለቡና ታሪካዊ ዳራ፣ ጠቀሜታዎች እና የጎንዮሽ ጉዳቶች በአጭሩ አቅርቧል።
ዩክሬን እና ሩሲያ ሱዳን ውስጥ በእጅ አዙር ጦርነት እያካሄዱ ነው?
መስከረም 2016 ዓ.ም. ላይ በማይገመት ቦታ፣ ጨርሶ ሊገመቱ በማይችሉ ሁለት መሪዎች መካከል ስብሰባ ተደረገ። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪ ከሱዳኑ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር በአየርላንድ በሚገኝ አየር ማረፊያ መገናኘታቸው ብዙዎችን አስደንቆ ነበር።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች
የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው። ተቋሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹላ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል።
አነጋጋሪ ጉዳይ
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ
በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እና በተቀናጁ ዘመቻዎች ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ያደረገው ምርመራ አረጋገጠ።
አባ ገዳ ጎበና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ተናገሩ
የቱለማ አባ ገዳ የሆኑት አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ከወጪ እስከ ችርቻሮ ንግድ ዘርፍ መግባታቸው በረከት ወይስ ስጋት?
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ ሆነው የኖሩ የምጣኔ ሃበት ዘርፎችን እየከፈተች ነው። በቅርቡ ድግሞ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ተጠብቀው የነበሩት የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የአገር ውስጥ ባላሃብቶችን እና ነጋዴዎችን ከገበያ ያስወጣል የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ውድድርን በመፍጠር ለሸማቾች አማራጮችን ያቀርባል የሚሉ አሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ይከሰታል? በወታደራዊ አቅምስ ይመጣጠናሉ?
ኢራን እና እስራኤል እስካለፈው ሳምንት ድረስ በእጅ አዙር እንጂ በቀጥታ ግጭት ውስጥ ገብተው አየውቁም። አሁን ግን በሚሳኤል እና በድሮኖች አንደኛው በሌላኛው ላይ ግልጽ ጥቃት መፈጸም ጀምረዋል። ለመሆኑ እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ሊከሰት ይችላል? ሁለቱ አገራትስ በወታደራዊ አቅም ምን ያህል ይመጣጠናሉ?
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውጥረት እንዳይባባስ ለውይይት ክፍት እንዲሆኑ የቡድን ሰባት አገራት ጠየቁ
ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር በተፈረመ የመግባቢያ ስምምነት ውዝግብ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁሉንም የውይይት መንገዶች ክፍት እንዲያደርጉ የቡድን ሰባት አገራት ጠየቁ።
ከራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እና አመራሮች ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ናቸው?
በአወዛጋቢዎቹ የራያ አካባቢዎች ያለውን ባለው አለመረጋጋት ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቆቦ፣ በሰቆጣ፣ በወልዲያ እና በሐሙሲት ከተማዎች መጠለላቸውን ተፈናቃዎች እና በአማራ ክልል የተሾሙት የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ረሃብ ባንዣበበባት ሱዳን ከጦርነቱ ከሚሸሹ ሰዎች የሚሰሙ የግድያ እና የመደፈር ታሪኮች
አንድ ዓመት ያለፈው የሱዳን የእስር በርስ ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለው ጦርነት ሚሊዮኖችን አፈናቅሏል። ፤ሎች ሚሊዮኖች ደግሞ በረሃብ አፋፍ ላይ ከሚገኙባት ሱዳን ዘግናኝ የግድያ እና ፆታዊ ጥቃት ታሪኮች እየተሰሙ ነው።
ኢትዮጵያ፡ 56 በመቶ የሚሆኑ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፊደል መለየት እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ
በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ክፍል ተማሪች 56 በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ጥናት አመልክቷል። አገልግሎቱ በጥናቱ ተሳተፊ ካደረጋቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉ 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤፋ ጉርሙ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው።
በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች
ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች።
ኢራን እና እስራኤል ለምን ደመኛ ጠላቶች ሆኑ?
ኢራን ከግብፅ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ እስላመዊ አገር ነበረች። ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ ይህ ግንኙነት ተበላሽቶ ከአምስት አስርታት በላይ በጠላትነት እየተያዩ ቆይተዋል። ለመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ደመኛ ጠላትነት ለምን ተሸጋገረ?
በኬንያ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የአገሪቱ ኢታማዦር ሹም እና ሌሎች መኮንኖች ሞቱ
የኬንያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ይበሩበት የነበረው ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሕይወታቸው ማለፉን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ።
በጎርፍ በተጥለቀለቀችው ኤምሬትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ከሁለት ቀናት በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በሌሎች አገራት አውሎ ንፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል። በዩናይትድ አረብ ኤምሬት ታሪክ በ75 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ መሆኑ የተመዘገበለት ከባድ ዝናብ ተሽከርካሪዎችን ጠርጎ ከመውሰድ በተጨማሪ የተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳቶች አድርሷል። ለመሆኑ በነዚህ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ከየፈርጁ
በዩናይትድ ኪንግደም የጥገኝነት ጠያቂዎች ሆቴል ውስጥ የምትኖረው የብስክሌት ሻምፒዮኗ ትርሐስ
በኢትዮጵያ የብስክሌት ሻምፒዮናዋ ትርሐስ ተስፋይ በለንደን ትልቁ የብስክሌት ውድድር ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ናት። ትርሐስ ለስደት ተዳርጋ በምዕራብ ለንደን ጥገኝነት ጠያቂዎች በሚኖሩበት ሆቴል ውስጥ ነው የምትኖረው።
ወደ ባንኮች ያዘዋወሩትን ገንዘብ መመለስ ባለመቻላቸው አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት ተማሪዎች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገንዘብ ዝውውር ሥርዓቱ ላይ አጋጥሞት በነበረው ችግር ምክንያት በርካታ ደንበኞቹ የራሳቸው ያልሆነ የገንዘብ መውሰዳችን አሳውቆ አብዛኛውን ገንዘብ ማስመለሱንም መግለጹ ይታወሳል። ያልመለሱትን ደግሞ ፎቷቸውን ጨምሮ መረጃቸውን በተለያየ መንገድ ይፋ አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ውስጥ ስማቸው በስፋት ሲነሳ የነበሩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውደቃቸውን እየተናገሩ ነው።
ታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ በስለት ተወግተው ዐይናቸውን ያጡባትን ዕለት ሲያስታውሱ
ታዋቂው ደራሲ ሰር ሳልማን ሩሽዲ ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ባሳተሙት መጽሐፋቸው ምክንያት ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ሲሰነዘርባቸው ቆይተው ከሁለት ዓመት በፊት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በዚህም አንድ ዐይናቸውን ያጡ ሲሆን፣ ያቺን ዕለት ሲያስታውሱ የዐይን ብርሃናቸውን ማጣታቸው ማጣታቸው በእጅጉ እንደሚያንገበግባቸው ይናገራሉ።
ወደ የኦሮሚያ አካባቢ አንመለስም ያሉ ተፈናቃዮች የምግብ እርዳታ “ተከለከልን” አሉ
የደኅንነት ስጋት አድሮባቸው ዳግም ወደ ደብረ ብርሃን የተመለሱ እና ቀድሞውኑም ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑ በሺህ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የምግብ እርዳታ እንዳይሰጣቸው መከልከሉን ተፈናቃዮች እና አስተባባሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አወዛጋቢ የሚባሉት የአሲሪያን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አቡን ማር ማሪ ኢማኑዔል ማን ናቸው?
አቡነ ማር ማሪ ያደጉት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ሲሆን፣ በልጅነታቸው ነው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ አውስትራሊያ ያቀኑት። ክራይስት ዘ ጉድ ሼፐርድ ቤተ-ክርስቲያን ድረ-ገፅ እንደሚጠቁመው አባ ማር ማሪ ኢማኑዔል በአውሮፓውያኑ 2009 ቄስ፤ ቀጥሎ ደግሞ በ2011 አቡን ሆነው ተቀብተዋል።
ከ50 በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በሱዳን ኃይሎች እንደምርኮኛ መያዛቸው ተነገረ
በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ ለማቋረጥ ሲሞክሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወጣት ስደተኞች ለአንድ ዓመት በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በሚገኙ ተዋጊ ኃይሎች እንደ ምርኮኛ ተይዘው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።
ኢራን በእስራኤል ላይ በፈጸመችው ጥቃት ማን አተረፈ? ማንስ ከሰረ?
ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት ኢራን በእስራኤል ላይ በሚሳኤል እና በድሮኖች የፈጸመችው ጥቃት በመላው ዓለም ስጋት ፈጥሯል። ሁለቱም አገራት ከዚህ ፍጥጫ የሚፈልጉትን ዓላማ ለማሳካት ጥረት እያደረጉ ሲሆን፣ ለመሆኑ ከቅዳሜው ጥቃት ኢራን ወይስ እስራኤል አትራፊ ሆኑ?
አደገኛ በመሆኑ ከገበያ እንዲሰበሰብ ስለተባለው የህጻናት የሳል ሽሮፕ ምን እናውቃለን?
ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት የተወሰኑ የጆንሰን ኤንድ ጀንሰን የሳል ሽሮፖች ከገበያ እንዲሰበሰቡ አዘዋል። “እጅግ ከፍተኛ” መርዛማ እና የመግደል አቅም ያለው ዳይትሊን ግላይኮል የተባለውን ንጥረ ነገር በምርመራ እንዳገኙበት ገልጸዋል።
ጆ ባይደን ከዶናልድ ትራምፕ፡ ለፕሬዝዳንትነት አሸናፊውን የሚለዩ አራት ወሳኝ ነጥቦች
ትራምፕ ዘመቻቸውን ወደ ኋላ ሊጎትትባቸው የሚችለው ጉዳይ እየቀረበባቸው ያለው ክስ ነው። አልፎም የሚያሰሟቸው አወዛጋቢ ንግግሮች እና ያለፈውን ምርጫ ውጤት ለመቀበል ማመንታታቸው እንደ ድክመት ይነሳባቸዋል። ባይደንም ቢሆኑ ከድክመት ነፃ አይደሉም።
ቻይናዊ ሯጭን አሸናፊ ያደረጉት ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች እንዲሁም አሸናፊው ሜዳልያቸውን ተነጠቁ
በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ቻይናዊ ሯጭን ሆን ብለው አሸናፊ አድርገውታል የተባሉት ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች እንዲሁም አሸናፊው ቻይናዊ ሜዳልያቸውን ተነጠቁ።
በእስራኤል ጥቃት በአንድ ላይ ስለተገደሉት የሐማስ መሪ ልጆች እና የልጅ ልጆች ምን እናውቃለን?
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ ሦስት ልጆች እና አራት የልጅ ልጆቻቸው ረቡዕ ዕለት እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ተገድለዋል። ለመሆኑ የተገደሉት የሃንዬህ ልጆች በሐማስ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ አላቸው?
አጃኢብ!
ቡና እንዴት በዓለማችን በብዙዎች የሚወደድ አነቃቂ ፍሬ ሊሆን ቻለ?
እንቅልፍ ከማትተኛው የኒው ዮርክ ከተማ እስከ ኢትዮጵያ ተራሮች ድረስ ዝናው የናኘ ነው፤ ቡና። ሚሊዮኖች ሳይጎነጩት መዋል አይቻላቸውም። ቡና ለ15 ክፍለ ዘመናት የሰው ልጆች ባህል ማዕከል ሆኖ ኖሯል። አንዳንዶች የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን አብርሆት ከቡና ነው የመነጨው ይላሉ።
ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን ከሥራ እና ከማኅበራዊ ግልጋሎቶች የሚያገል ምዝገባ ልትጀምር ነው
የኢትዮጵያ መንግሥት ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ምዝገባው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያለመ ነው የተባለ ሲሆን፣ በተለይ “ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ ትኩረት” እንደሚያደርግ ተነግሯል።
100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች የሚጋሯቸው 8 ሥነ-ልቦናዊ ባህሪያት
አብዛኛዎቹ 100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች አሁንም ጤናማ ናቸው፤ ጥንካሬያቸው ያስቀናል፤ ከሰው ለማውራት ጉጉ ናቸው። በእንግሊዝኛው ሴንቴናሪያንስ ይባላሉ። 100 ዓመት ያለፋቸው የዕድሜ ባለፀጋዎች ናቸው። እነዚህ የዕድሜ ባለፀጎች የሚያመሳስሏቸው በርካታ የጋራ ባህሪያት አላቸው።
በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችንን ስለ አደጋዎች እንዴት ማስተማር እንችላለን?
ዕድሜ ሲጨምር ስለ አደጋ ያለ ግንዛቤም ያድጋል። ልጆች ግን ሊገጥማቸው የሚችለውን አደጋ ባለማወቅ በቀላሉ ለጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ። ታዲያ ልጆችን ስለ አደጋ እና ቅድመ ጥንቃቄ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው? በተለያየ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆችን ስለ አደጋ ማስተማር የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ።
አንድ ሠራተኛ በመቀለ አይደር ሆስፒታል ውስጥ በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ባላቸው የህክምና መሳሪያዎች ላይ ጉዳት አደረሰ
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ባልደረባ በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያላቸው በርካታ የህክምና መሳርያዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገብረግዚአብሄር ለቢቢሲ ተናገሩ።
የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች መርከብ ማስለቀቂያ 5 ሚሊዮን ዶላር ተቀበልን አሉ
የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች አግተን የነበረውን የባንግላዴሽ ባንዲራን የምታውለበልብ መርከብ እና ሠራተኞቿን ለማስለቀቅ 5 ሚሊዮን ዶላር ተቀበልን አሉ።
እስራኤልን የጦር መሳሪያ የሚያስታጥቋት አገራት እነማን ናቸው?
እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው ጥፋት ምክንያት በዘመናዊ መሳሪያዎችን በሽያጭ እና በድጋፍ ሲያስታጥቋት የነበሩት ምዕራባውያን አገራት የሚያቅርቡላትን ጦር መሳሪያ እንዲያቆሙ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በእስራኤል ላይ የመሳሪያ አቅርቦት ማዕቀብ እንዲጣል ወስኗል። ለመሆኑ እስራኤል ለሠራዊቷ የምታስታጥቃቸውን የጦር መሳሪያዎች ከየኞቹ አገራት እና በምን መልኩ ታገኛለች?
ቪዲዮ, ቢቢሲ ያጋለጠው የአፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ሰቆቃ በባሕረ ሰላጤዋ አገርርዝመት, 5,25
በባሕረ ሰላጤው አገራት ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ይገኛሉ። ኑሮን ለማቃናት ወደ አረብ አገራቱ ያቀኑት አፍሪካውያን ግን ሥራ እና ኑሮ ቀላል አልሆነላቸውም። አብዛኞቹ በአሠሪዎቻቸው ጉልበታቸው የሚበዘበዝ፣ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት የሚፈጸምባቸው፣ በረሃብ የሚሰቃዩ እና ሌሎችም በደሎች ይደርስባቸዋል። ከእነዚህ መካከልም በተለይ ኦማን ውስጥ በሚገኙ አፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ሠርቷል።
ባለፉት ዓመታት በእስራኤል ከተገደሉ የኢራን ተመራማሪዎች እና የጦር መኮንኖች ዋነኞቹ
እስራኤል ጠላቶቼ ከምትላቸው መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች - ኢራን። ኢራንም ብትሆን ‘አጥፊዬ’ ከምትላቸው አገራት መካከል ቀን ከሌት በዐይነ ቁራኛ የምትጠብቃት እስራኤልን ነው። እስራኤል ባለፉት ዓመታት ጥቂት የማይባሉ የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቶችን እና የጦር ጄኔራሎችን ኢላማ አድርጋለች።
በአንድ ጨዋታ 31 ግቦች የተቆጠሩበት ግብ ጠባቂ
በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ሁሉም ተሰላላፊዎች ለቡድኑ ድል እና ሽንፈት ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ የግብ ጠባቂን ያህል ግን የጎላ አይሆንም። በተለይ ደግሞ አንድ ቡድን በርካታ ግቦች ተቆጥረውበት ሲሸነፍ የሁሉም ዐይን የሚያርፈው በረኛ ላይ ነው። ታዲያ በአንድ ጨዋታ ከሦስት አስሮች በላይ ጎለረ ያስተናገደ በረኛ ምን ይሰማው ይሆን?
ኢራን በበርካታ ግጭቶች ውስጥ ለምን ትሳተፋለች?
እስራኤል በጋዛ እያካሄደችው ያለው የማያባራ ጥቃት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በቀጣናው ሌላኛው እየተነሳች ያለች አገር ኢራን ናት። ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ እየተጫወተችው ያለው ሚና የዓለምን ቀልብ እየሳበ ይገኛል።
በገዛ ጓደኛዋ ፎቶዋ በረቀቀ ሁኔታ ተቀናብሮ የወሲብ ቪዲዮዎች ድረ-ገጽ ላይ የወጣባት ወጣት
በ20ዎቹ የእድሜዋ አጋማሽ ላይ የምትገኘው ጆዲ ለጠላቷ የማትመኘው ነገር ገጥሟታል። ፎቶግራፏ የእውነት በሚመስል ሁኔታ ተቀነባብሮ ልቅ የወሲብ ፊልሞች በሚታዩባቸው ድረ-ገጾች ላይ ምሥሏ ተሠራጭቶ አግኝታዋለች። ከዚህ እኩይ ተግባር ጀርባ ያለው ደግሞ የቅርቤ የምትለው ጓደኛዋ መሆኑ ጉዳቷን የከፋ አድርጎታል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
ቪዲዮ, በበርካታ አገራት ከተሞችን በማውደም አሳሳቢ አደጋን እየጋረጠ ያለው የመሬት መንሸራተትርዝመት, 3,44
በዚህ ዘመን የመሬት መንሸራተት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ክስተት ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በደቡብ አሜሪካ እና በአፍሪካ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችም ለውድመት ሲዳረጉ፣ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። የመሬት መሸርሸር ተፈጥሯዊ ቢሆንም ሰው ሰራሽ ምክንያቶች እንዳባባሱት ባለሙያዎች ይገልጻሉ። በዚህም ሳቢያ በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ያሉ ከተሞች አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
ዛሬ በመላው ዓለም የሚከበረው የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
የምድር ቀን በመላው ዓለም ዛሬ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. (በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 22) በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ዓለም ይታሰባል። ይህ የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
የኢድ አል-ፈጥር በዓል ቀን የሚወሰነው እንዴት ነው?
1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ የሆነው የረመዳው ወር ሲጠናቀቅ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ትርጉም የሚሰጠው የኢድ-አልፈጥር በዓል ይከበራል።
የአእምሮ ጤና እክል የሆነው ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድን ነው? ለምንስ ከታዋቂው ሠዓሊ ጋር ተያያዘ?
በተቃራኒ የስሜት ጽንፎች ውስጥ መዋለል (ባይፖላር ዲስኦርደር) ከ100 ሰዎች ውስጥ በአንድ ሰው ላይ ይከሰታል። ስለዚህ የአእምሮ ጤና እክል ግንዛቤን ለማስፋት መጋቢት 21 በየዓመቱ የባይፖላር ዲስኦርደር ቀን ይታሰባል። ይህ ቀን ደግሞ የታዋቂው ሠዓሊ ቪንሰንት ቫን ጎ የልደት ቀን ነው። ዕለቱ ለምን ከእሱ ጋር ተያያዘ? ቫን ጎ ባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር ነበረበት?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ጁሊያን አሳንጅ ማን ነው?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ዊክሊክስ የተሰኘው ድረ ገጽ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ ከሰሞኑ የበርካታ መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።
ችላ ተብለው በአሳሳቢ ደረጃ በመላው ዓለም እየተስፋፉ የመጡት የአባላዘር በሽታዎች
እንደ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ በመላው ዓለም በየቀኑ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ይያዛሉ። ነገር ግን በትክክል በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ ምንድን ነው? ዓይነቶቹ እና ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ማንኮራፋት እንዴት ትዳርን እስከ ማፍረስ ሊያደርስ ይችላል? ምንስ መፍትሄ አለው?
የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ለሚያንኮራፋው እና ከጎን ለሚተኛ አካላዊ እና የአእምሮ ጤና ጉዳት ያስከትላል። ትዳር ሊያፈርስ ይችላል።
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
በረመዳን የፆም ወቅት የትኞቹን ዓይነት ምግቦች መመገብ፣ የትኞቹንስ መተው አለብን?
ረመዳን የፆም ወቅት ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው። ከማለዳ ጀምሮ አስከ ምሽት ድረስ ምግብ ሳይቀመስ የሚቆይበት የፆም ጊዜ የመጀመሪያ ቀናት ለአንዳንዶች ፈታኝ ነው። በፆሙ ወቅት መደበኛ እንቅስቃሴያችንን እያደረግን ያለድካም ለመቆየት የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በዚህ ወቅት ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ፤ የትኞችንስ ማስቀረት አለብን?
ራስን ማጥፋት የሚያበረታታው እና ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነው መርዝ ሻጭ በቢቢሲ ተጋለጠ
በዩናይትድ ኪንግደም ቢያንስ 130 ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተውበታል የተባለውን መርዝ የሸጠውን ዩክሬናዊ ቢቢሲ ተከታትሎ ደርሶበታል። ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው ይህ ግለሰብ ራስ ማጥፋትን የሚያበረታታበት እንዲሁም አገልግሎቱን የሚያስተዋውቅበት ድረ ገጽ አለው።
ማር ለጤናችን ምን ያህል ጠቃሚ ነው? መመገብ ያለባቸውስ እነማን ናቸው?
ከስኳር የሚጣፍጠው የተፈጥሮ ማር ብቸኛው የስኳር አማራጭ ነው? ለሁሉም ሰውስ በእኩል ይጠቅማል? ሕጻናትን ለመመገብስ የዕድሜ ገደብ አለው? የምንወስደው መጠንስ ምን ያህል መሆን አለበት? ለእነዚህ የበርካታ ሰዎች የዘውትር ጥያቄዎች የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት ጆ ልዊን ምላሽ አላቸው።
የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?
ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?